bablon ke coved melsi finali
bablon ke coved melsi finali

00:00:59
Views: 18
bablon ke coved melsi finali

about

 

About Ethiopian National Theater

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር

የቴአትር ቤቱ ተልዕኮ ራዕይ ስልጣን እና ተግባራት

ተልዕኮ

«የኢትጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦቸ ትውፊታዊና ልዩ ልዩ ትውን ጥበባትን በማጥናት ወጥነታቸውን ጠብቆ በማዘጋጀት በማበልፀግ በማስተዋወቅና ተደራሽ በማድረግ ለልማት እና ለመልካም ገፅታ ማዋል፡፡´

ራዕይ

በ2017 ኢትዮጵያ ትውፊታዊ ትውን ጥበባት ለምተው በባሕላዊ ህብረ ቀለማት በአፍሪካ ተጠቃሽና የታወቀ ቴአትር ቤት ማድረግ፡፡

አላማ

 • የኢትጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ሕዝቦች ትውፊታዊ ትውን ጥበባትን ማሳደግ፣መጠበቅና ማራመድ፣
 • በፈጠራ ጥበብ ውበት እያዝናኑ ቁም ነገር በማስተላለፍና የአስተሳሰብ ለውጥ በማምጣት ሕብረተሰቡ በሀገር ልማት፣በዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታና መልካም አስተዳደር በማስፈን እንቅስቃሴ ውስጥ ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆን የሚያበረታቱ ልዩ ልዩ ኪነጥበባዊ ስራዎችን በማዘጋጀት ማቅረብ”

የብሔራዊ ቴአትር ሥልጣንና ተግባር

 • የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ማንነት መገለጫ የሆኑትን ትውፊታዊ ኪነጥበባት ባህላዊ እሴታቸው ተጠብቆ እንዲበለፅጉ እና በመድረክ ተቀነባብረው በእኩልነት በአገር አቀፍ ሆነ በዓለማቀፍ ደረጃ እዲቀርቡ እና እንዲታወቁ ማድረግ፡፡
 • የብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦችን ትክክለኛ ባህላዊ ገጽታ የሚያንጸባርቁ ትውፊታዊ ትውን ጥበባትን ከምንጫቸው በማጥናትና በጽሁፍ፣በምስልና በናሙና ቁሳቁስነት በማደራጀት በመጠበቅ ለመጭው ትውልድ እንዲተላለፉና በአገልግሎት ላይ እንዲውሉ የማድረግ፣
 • የሀገሪቱን  የኪነ-ጥበብ እንቅስቃሴ ዕድገት ወደፊት ለማራመድ የዘርፉ ባለሙያዎች ኪነ-ጥበባዊ ስራዎቻቸውን በክልል፣በአገር ዓቀፍና በአለም ዓቀፍ መድረኮች እንዲያቀርቡ የቴክኒክ እና የመረጃ እገዛ የማድረግና የማበረታታት፣
 • የሀገሪቱን የኪነጥበብ እድገት ወደፊት ለማራመድ የሚያግዙ ሴሚናሮችን፣ ወርክሾፖችን፣ኮንፈረንሶችንና የምክክር መድረኮን የማዘጋጀትና የማካሄድ፣
 • በኪነጥበብ ዘርፍ የተሰማሩ ሙያተኞችና አመራሮችን አቅም ለማሳደግ የቴአትር፣ የሙዚቃ፣የውዝዋዜ፣የመድረክ አጠቃቀም እና የአመራር ስልጠና የመስጠት፣
 • ህብረተሰቡን ለልማት፣ ለሰላም፣ ለዲሞክራሲና ልማት  ለማነሳሳት ኪነጥበባዊ ብቃት ያላቸው ተውኔቶችና ሙዚቃዎችን  በማዘጋጀት በመድረክና አመቺ በሆኑ መገናኛ ብዙኃን የማቅረብ፣
 • ለኪነጥበብ ስራዎች ዝግጅት አገልግሎት የሚውሉ መድረኮችን የማደራጀት፣
 • በኪነጥበብ መስክ የተሰማሩ የፈጠራና የምርምር ባለሙያዎችን የማበረታታትና የመደገፍ፣
 • የሀገሪቱን ትውን ጥበባት ለአፍሪካ ህዝቦች በማስተዋወቅና የልምድ ልውውጦችን በማድረግ የአህጉሩን አንድነትና የባህል ትስስር የማጠናከር፣
 • ዓለም ዓቀፋዊ ህብረትና ወዳጅነትን ለማጎልበት የሌሎች አገሮች ኪነጥበባዊ ቡድኖችና ማስተናገድ እና ለኪነ ጥበባት እድገት በትብብር የመስራት፣
 • ከሚያቀርባቸው የቴአትርና የሙዚቃ ትርኢቶች እና ከሌሎች አገልግሎቶች የሚገኝ ገቢን የመሰብሰብ፣
 • የንብረት ባለቤት የመሆን፣ውል የመዋዋል፣በስሙ የመክሰስ እና የመከሰስ፣
 • ዓላማውን ከግብ ለማድረስ የሚያስፈልጉ ሌሎች ተግባራትን የማከናወን፡፡

ታሪካዊ ዳራ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር በባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ስር የተደራጀ ብቸኛው ብሔራዊ የትውፊታዊ ትውን ጥበባት፣ የቴአትር እና የሙዚቃ ማስፋፊያ እና ማልሚያ ድርጅት ነው፡፡

ሲቋቋም ቀዳማዊ ኃይለስላሴ ቴአትር የሚለው ስሙ ተቀይሮ በ1967ዓ/ም በአዋጅ በአሁኑ ስያሜው እንዲጠራ ሆኗል፡፡

ቴአትር ቤቱ 1200 ያህል መቀመጫዎች ያሉት ሲሆን የመድረኩ ስፋት ማናቸውንም ትላልቅ ትርዒቶች ማስተናገድ የሚችል ነው፡፡ በአዳራሹ ውስጥ ለንጉሠ ነገስቱ የሚሆን ልዩ እና የተሟላ የመመልከቻ ስፍራ ያለው ነው፡፡

አዳራሹ በሀገራችን እስከአሁንም ድረስ ቢሆን በድምፅ፣ በመብራቶቹና በስቴጅ ማሽነሪ ቴክኖሎጂው የተሻለ ብቃት ላይ የሚገኝ ነው፡፡

ቴአትር ቤቱ ስራ ሲጀምር በቴአትር እና በዘመናዊ ሙዚቃ ቢሆንም ብዙ ሳይቆይ የኢትዮጵያን ብሔር ብሔረሰቦች ሙዚቃዎችን እና ጭፈራዎችን ማቅረብ ጀምሮ እስከ አሁንም ይህንን ተግባሩን እየፈፀመ ይገኛል፡፡

ቴአትር እንደ ዛሬ ዝነኛ ባልነበረበት ዘመን በቴአትር ቤቱ በይበልጥ ይቀርብ የነበረው የምዕራባውያን ፊልሞች ነበር፡፡ በየእለቱ መድረኩን ይቆጣጠር የነበረው ፊልም ቦታውን ለቴአትር አስረክቦ ዛሬ በቴአትር ቤቱ በሳምንት ሰባት ቴአትሮች ይቀርባሉ፡፡

የሀገረሰብ ሙዚቃ‹ የዘመናዊ ሙዚቃ ኮንሰርት፣ የተለያዩ ዓይነት ቴአትሮች፣ሠርከስ፣ ሙዚቃዊ ድራማዎችን፣ አስተናግዷል መድረኩ እንዲሁም ከአውሮፓ፣ ከእሲያ፤ ከአሜሪካ እና ከአፍሪካ ሀገራት የመጡ የባህል ትርዒቶች ይቀርቡ ነበር፡፡ አሁንም እየቀረቡ ነው፡፡

በሣምንት በአማካይ በቴአትር እና በፊልም ከ5000 በላይ ተመልካቾችን ያስተናግዳል፡፡ እየተካሄደ ባለው ቢፒአር የትርዒት ዓይነት እና መጠን በመጨመር ይህ የተመልካች ቁጥር ይጨምራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ቴአትር ቤቱ አነስተኛውን የመግቢያ ዋጋ ነው የሚያስከፍለው፡፡

መነሻ /origin/

ኢትዮጵያ ከኢትዮ-ጣሊያን ጦርነት በኋላ በሯን ለምዕራቡ ዓለም እና ለሥልጣኔ በመክፈቷ በሀገሪቱ ከተሞች አዳዲስ ባህሎች መታየት ጀምረው ነበር፡፡ በተለይም የምሽት ክለቦች፣ ፊልሞች፣ሙዚቃዎች፣ መፅሔቶች በወቅቱ አዲስ አበባን አጥለቅልቀዋት በነበሩት የውጭ ዜጎች አማካኝነት እየተስፋፉ ነበር፡፡

ይህ የባህል ወረራ ያሳስባቸው የነበሩ የጊዜው ምሁራኖች እና አገር ወዳዶች የሀገራችንን ሙዚቃ እና ቴአትር በማስተዋወቅ የባህል ወረራውን ለመቋቋም ጥረት ሲያደርጉ ቆይተዋል፡፡ የዚህም ጥረታቸው የመጀመሪያ ውጤት በአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት ስር የተደራጀው የቴአትር እና የሙዚቃ ቡድን ነበር፡፡

እንደ ዮፍታሄ ንጉሴ፣ አፈወርቅ አዳፍሬ የመሳሰሉ የተውኔት፣ የግጥም እና የዜማ ደራሲዎች በፈለቁበት በዚህ ዘመን ይደረግ በነበረው የሙዚቃ እና የቴአትር እንቅስቃሴ ተጠቃሽ ነው፡፡

በ1948ዓ/ም የቀዳማዊ ኃይለስላሴ የዘውድ በዓል በደመቀ ሁኔታ እንዲከበር መወሰኑ በሀገራችን ሙያዊ የሆነ ቴአትር ቤት እንዲመሠረት ጥሩ አጋጣሚ ሆነ፡፡ በንጉሠ ነገስቱ ፈቃድ፤ በአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት ባለቤትነት የቀዳማዊ ኃይለስላሴ ቴአትር በ1948ዓ/ም ተመሠረተ፡፡

ቴአትር ቤቱ ህዳር 3/1948ዓ/ም ተመርቆ ከፈረንሳይ ሀገር በመጣ ባለ ትርዒት እና ዳዊት እና ኦርዮን ከተባለው ቴአትር አንድ ክፍል በማሳየት ነበር፡፡

ቴአትር ቤቱን ለመሥራት አስቀድሞ ተወጥኖ የነበረው አቡነ ጴጥሮስ ሐውልት ፊት ለፊት የዛሬው ማዘጋጃ ቤት የሚገኝበት ስፍራ ላይ ነበር፡፡ ሆኖም የንጉሠ ነገስቱ 25ኛ ዓመት የንግስና በዓል ስለተቃረበ እና ለዚሁ አጀብም ቴአትር ቤቱ እንዲደር ስለተፈለገ ለዚህ የተገኘው አማራጭ ቀድሞ ጣሊያን ሲኒማ ማርኮኒ የተባለ ሲኒማ ቤት ለመክፈት አስቦ በጅምር ያቆመውን ህንፃ ወደ ቴአትር ቤት በመቀየር ነበር፡፡ አዳራሹ ለቴአትር ስራ እንዲመች ማስተካካያ የዲዛይን ሥራ እንዲሰራለት ተደርጎ ዛሬ የምናየው ህንጻ ተገንብቶአል፡፡

ሥራው በአራት ወራት ጊዜ ውስጥ 3-5 ሚሊዮን ብር ወጪ ተጠናቋል

አዳራሹ 1200 መቀመጫዎች ሲኖሩት 364 ሜትር ካሬ ስፋት ያለው መድረክ፣ ሰፊ ኦርኬስትራ ፒት መልበሻ ክፍሎች፣ ሰፊና ውብ ፏዬ፣ መዝናኛ እና ለቴአትር ቤቱ ግርማ ሞገስን የሚያጎናፅፉ ልዩ ልዩ ቅርፆችም አሉት፡፡ በቅርቡም የአዳራሽ ኮርኒስ እና የጣራ ለውጥ፣ ተጨማሪ የመልበሻ፣ የመፀዳጃ እና የመለማመጃ ክፍሎች ተገንብተውለታል፡፡

ቴአትር ቤቱ ያለው ግርማ ሞገስ እና ውበት በከተማው ከሚጎበኙ የቱሪስት መስህቦች አንዱ እንዲሆን አድርጎታል፡፡

የሚገኘውም የከተማዋ ማዕከል ነው ተብሎ በሚታመነው በቸርችል ጎዳና፣ ባንኮች፣ ኢንሹራንሶች፣ ሆቴሎች እና ልዩ ልዩ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት በሚገኙበት ሰፈር ነው፡፡

ወቅታዊ ስራዎች

በአሁን ወቅት 5 ቴአትር በሳምንቱ  ቀናት ለህዝብ እየቀረቡ ይገኛል፡፡ ዘወትር አርብ ‹‹

አልቃሽና ዘፋኝ›› እና ዘወትር ሐሙስ የሚቀርቡ ‹‹

የኮከቡ ሰው›› ቴአትር ቤቱ ቴአትር ተቋማትን ለማበረታታት በያዘው ፕሮግራም መሠረት እየቀረቡ የሚገኙ ናቸው፡፡

ዘወትር ረቡዕ ‹‹

የኛ ሰፈር›› ይቀርባል፡፡ ይህ ተውኔት በህዝብ ዘንድ በጣም ተወዳጅ ስለሆነ በድጋሚ የቀረበ ነው፡፤ አሁንም ተወዳጅ ሆኑ እየዘለቀ ነው፡፡

እሁድ ‹‹ባቢሎን በሳሎን›› ተውኔት እየቀረበ ነው፡፡

 

ትውፊት ላይ ተመሠረት ተውኔት

ይህን ቴአትር ቤቱ ከሌሎች ቤቶች የሚለየው አንዱ እንቅስቃሴ ‹‹ትውፊት›› ላይ ያለው ትኩረት ነው፡፡ ምንም እንኳን በዚህ አቅጣጫ ብዙ ተሰርቷል ባይባልም ቴአትር ቤቱ እንደ አቅጣጫ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡ የባላገር ፍቅር፣ አዳብና፣ ጉማ የመሳሰሉ ትውፊት ላይ የተመሠረቱ ተውኔቶች ለህዝብ ቀርበው ነበር፡፡

                     አድራሻዎቻችን

ተ.ቁ

የዳይሬክተር ስም

ዳይሬክቶሬት

ቢሮ ቁጥር

ስልክ

1

አቶ ማንያዘዎል እንዳሻው

ዋና ዳይሬከተር

   

2

አቶ ደስታ አስረስ 

የቴአትር ዳይሬክቶሬት

 

 

3

አቶ ወሰንየለህ መብረቁ

የሙዚቃ ዳይሬክቶሬት

 

 

4

አቶ ፋነታሁን ኬሬቦ 

የት/ት/ጥ/ጥናት፣ምርምርና ስልጠና ዳይሬክቶሬት

 

 251115547876

5

ወ/ሮ ዝናሽወርቁ በላይ

የፖ/ዕ/ዝ/ክ/ግ/ ዳይሬክቶሬት

 

 

6

አቶ አክሎግ ብሩ

የለ/መ/አ/ጉ/ክ/ድ ዳይሬክቶሬት

 

 

7

ወ/ሮ ሙሉመቤት

የግዥ ፋ/ን/አ/ ዳይሬክቶሬት

 

 

 

አቶ ውበቱ  ወርቁ

የሰ/ሀ/ል/አ/ ዳይሬክቶሬት

 

 

 

አቶ ቢኒያም ጌታቸው

የኢ/ቴ/መ/ስ/አ ዳይሬክቶሬት

 

 

10

አቶ ተመስገን ታደሰ

የውስጥ ኦዲት ዳይሬክቶሬት

 

 

 

ወ/ሮ ሰላም ዞይብ

የሴ/ወ/ጉ ዳይሬክቶሬት

 

 

 

ወ/ሮ ኩሪ

የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት

  

 0115547696

 13

አቶ አክሊለ ጽጌ

የፕ/ፕ/ፕ እና ደ/አ ዳይሬክቶሬት

 

 0115154920