bablon ke coved melsi finali
bablon ke coved melsi finali

00:00:59
Views: 18
bablon ke coved melsi finali

ነሀሴ 7 ቀን 2013
 
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ከሐምሌ 26 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ለሁለት ወራት የሚቆይ የቴአትር እና
የሙዚቃ ስልጠና ከተለያዩ ክልሎች፤ ከተሞች እና ከአዲስ አበባ ለተወጣጡ ሠልጣኞች በመሰጠት ላይ ይገኛል፡፡
በቴአትር ዘርፍ "የቴአትር ትወና" የሚለው ጽንሰ ሀሳብ በአርቲስት አለማየሁ ታደሰ፣ "የቴአትር ዝግጅትና
ፕሮዳክሽን" በአርቲስት ሳሙኤል ተስፋዬ "የተውኔት ድርሰት አጻጻፍ" ደግሞ በአቶ ብርሃኑ ተስፋ በመሰጠት
ላይ ይገኛል፡፡ በሙዚቃው ዘርፍ አቶ ደረጀ ተክሉ እና አቶ ሀብታሙ ደምሴ ሙዚቃ መሳሪያን ፤እንዲሁም
አርቲስት ዝናቡ ገ/ስላሴ እና አቶ አብይ መንበሩ የድምጻዊያንን የድምጽ አወጣጥ ዘዴ በተመለከተ ተግባራዊ
ስልጠና በመስጠት ላይ ይገኛሉ፡፡የትውን ጥበባት ስልጠና ጥናትና ምርምር ዳይሬክተር አቶ ፋንታሁን ኬሬቦ
እንደገለጹት ሰልጠኞቹ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር የሚቀርቡ የኪነጥበብ ዝግጅቶችን በነጻ የሚታደሙ
ሲሆን በቀጣይ በብሔራዊ ቴአትር መድረክ ላይ ተግባራዊ ልምምድ ይሰጣቸዋል ብለዋል፡፡
ይህ ሙያዊ የክረምት ስልጠና ላለፉት ስድስት አመታት በተለያየ ምክንያት ተቋርጦ የነበረ ሲሆን ዘንድሮ
እንደገና የጀመረ ነው ያሉት ዳይሬክተሩ ስልጠናው እየተሰጠ ያለው የእድገት በህብረት ትምህርት ቤት እና
የልደታ ክ/ከተማ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ባደረጉት የማስልጠኛ ቦታ ትብብር መሆኑን ጠቁመው ሰልጣኞች
በከፍተኛ ኃላፊነት ስልጠናቸውን ጨርሰው ለምረቃ እንዲበቁ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡
ስልጠናውን እየወሰዱ ያሉት ሰልጣኞች በበኩላቸው በሰጡት አስተያየት የስልጠናው ሂደት እውቀትና
ክህሎትን የሚያስጨብጥ እና በጣም አስደሳች ነው ብለዋል፡፡