አዲስ በአፈፃፀም ምዘናና እና በፌዴራል ሠራተኞች እዋጅ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ። በ2018 በጀት ዓመት ግማሽ ዓመት የሥራ ክንውን ሪፓርት ቀረበ።
ጥር 16 ቀን 2018 ዓ/ም
አዳማ
ለኢትዮጽያ ብሔራዊ ቴአትር ለየዘርፉ ሥራ አሥፈፃሚዎች አና ቡድን መሪዎች አዲስ በሚተገበርው የሥራ አፈፃፀም ምዘና አና በፌዴራል መንግሥት ሠራተኞች አዋጅ ቁጥር 1353 /2017 እና አዋጁን በማስፈፀም በወጣው ምልመላና መረጣ አፈፃፀም መመሪያዎች ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተስጠ።
ስልጠናውን የሰጡት በሲቩል ሰርቪስ ኮሙሽን የሥራ አመራር ዴስክ አቶ ሳዱዲን ተማም ሙሱ እና የሰው ሀብት ሕግ ስምሪት ባለሞያ አቶ አየለ ደምሴ ናቸው።
በስልጠናው ስለእፈፃፀም ምዘና ዓላማ፣ና አተገባበር ሠራተኞች ሌከተሏቸው በሚገባ የሥራ ባህል ፣መፍትሄ አፍላቂነት፣ግብረገብነት፣ ግልፅንት፣ እውነተኛነት የመሳሰሉት ዕሴቶች ከሥራ ውጤትና ከሥራ አፈፃፀም ጋር ያላቸው መስተጋብር ተዳሷል።
በዕለቱ የ 2018 ዓ/ም በጀት ዓመት የመጀመሪያው ግማሽ ዓመት ሪፖርት በስትራቴጂክና ዕቅድ ሥራ አስፈፃሚ በአቶ በየነ ጎንፉ የቀረበ ሲሆን የቴአትር ቤቱ ዋና ዳይሬክተር ዕጩ ዶ/ር ክቡር አቶ ባረከ ታደስ በቀጣይ ሊተገበሩ በሚገባቸው ሥራዎች ላይ አቅጣጫ ስጥተዋል።
የወላጅ ምርቃት
የታላቁ ቤተ ተውኔት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ልዑካን ቡድን የመኤኒት ማህበረሰብ የፍቅር ፣ የሰላም ፣ የእርቅና የምርቃት ጥሪ ተቀብሎ ተቋማዊ ተልዕኮ ለማሳካት ከጥር 04/2018 ዓ/ም ጀምሮ ውሎ እያደረ በአየር ተጉዞ ረጅሙን የየብስ ጉዞ ሲያደርግ ቆይቶ እነሆ ደቡብ ምዕራብ ክልል ምዕራብ ኦሞ ዞን ጎልድያ በጀሙ ሰማይ ስር በተፈጥሮ ልምላሜ ተሞሽሮ ዲጊያ ቴአትር እትብቱ በተቀበረበት ምድር በወላጆቹ ፊት በታላቅ ድምቀት ተመረቀ !!! አሻም ዞጊያ !!!
ታላቅ ሲንፎኒ ኦኬስትር ኮንሰርት ቀረበ
ታላቅ ሲንፎኒ ኦኬስትር ኮንሰርት ቀረበ፡- ታህሳስ 23 ቀን 2018 ዓ/ም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር 70ኛ ዓመትን እና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 75ኛ ዓመት ምሥረታ የአልማዝ ኢዩቤልዩ በዓልን ምክንያት በማድረግ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ያሬድ የሙዚቃ ት/ቤት እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር የስትሪንግ ኦርኬስትራ በጋራ ታላቅ ሲነፎኒ ኦኬስትራ ኮንሰርት አቀረቡ፡፡ በዕለቱ የሙዚቃ ተመራማሪና ባለሞያ የኢትዮጵያ ቤተመጽሐፍትና ቤተመዛግብት አገልግሎት ዋና ዳይሬክትር አቶ ሰርጸፍሬ ስብሀት እና ጥሪ የተደረገላቸው በርካታ የሙዚቃ አፍቃሪያን ተገኝተዋል፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ዋና ዳይሬክተር ዕጩ ዶክተር ክቡር አቶ ባረከ ታደሰ በመክፈቻ ንግግራቸው የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን የአንጋፋዎቹ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትርና የአዲስ አበባ ዩነቨርስቲ መሥረታ በዓልን ምክንያት በማድረግ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ስለተዘጋጀው ሲንፎኒ ኦርኬስትራ ኮንሰርት ባለሞያዎቹን አመስግነዋል፡፡ በቀጣይም እንዲህ ላለ የትብብር ሥራ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር በሩ ክፍት እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር የሙዚቃ ዋና ሥራ አሥፈጻሚ ወ/ት ግራሴላ ሌዊጂ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር እና ያሬድ ሙዚቃ ትምሕርት ቤት በታሪክ ያላቸውን ጥብቅ ግንኙነትን አስታውሰው በዕለቱ የነበረው ዝግጅት ቀጣይ ጥምረታችንን አመላካች ነው ብለዋል፡፡ ሲነፎኒ ስትሪንግ ኦኬስትራው ካቀረበው ኮንሰርት ውስጥ የኢትዮጵያ ብሔራዊ መዝሙር ኮንዳክተር ሰለሞን ሉሉ፤" እረኛው ባለዋሽንት" (ፕሮፌሰር አሸናፊ ከበደ ፡አክሊሉ ዘውዴ) ‹‹የልቤ ጉዞ›› ኮንዳክተር (አማኑኤል ቡሌ ፤ረዳት ፕ/ሮፌሰር አክሊሉ ዘውዴ) የአስቴር አወቀ ‹‹ጠይም ዘለግ ያለ›› ‹‹ የክቡር ዶ/ር የጥላሁን ገሠሠ ‹‹እንኳን ቆሜ ብቀበርም..›› ኮንዳክተር ዶ/ር ዕዝራ አባተ ‹‹የተነቃቃ ስሜት›› በረዳት ፐሮፌሰር አክሊሉ ዘውዴ የተቀመሩ ሥራዎች የቀረቡ ሲሆን የዕለቱን ሲነፎኒ ኦኬስትራ ኮንሰርት በ ረ/ፕ አክሊሉ ዘውዴ መራሒ ሙዚቃ መሪነት ቀርቧል፡፡
ጥቂት ስለ ኃይለማሪያም ሰይፉ
ጥቂት ስለ ኃይለማሪያም ሰይፉ በተለይም በሕፃናት ቴአትር ጅማሬ ላይ ሥሙ የመጀመሪያው ረድፍ የሚገኘው ኃይለማሪያም ሰይፉ በቀድሞው ሸዋ ጠቅላይ ግዛት በተጉለትና ቡልጋ አውራጀ ቅንብቢት በሚባል አካባቢ ሚያዚያ 21 ቀን 1952 ዓ/ም ተወለደ ፡፡ በራስ ቴአትር፣ በሐገር ፍቅር ቴአትር በአዲስ አበባ ባሕል ማስታወቂያ ቢሮ፣ በማስታወቂያና ባሕል ሚኒስቴር፣ በወጣቶች ባሕልና ስፖርት ሚኒስቴር፣እንዲሁም በጡረታ እረፍት እስከተገለለበት ጊዜ ድረስ በታለቁ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር አገልግሏል ፡፡ የሕፃናት ቴአትርን በመፃፍ ለመድረክ አበቅቷል፡፡ከነዚህ ውስጥ "አንበሴ" 1975 በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር፣"ዶዮ" 1981 በራስ ቴአትር "የእንቁላሉ ወፍጮ"1983 ሕጻናትና ወጣቶች ቴአትር ለዕይታ ያበቃቸው ናቸው፡፡ ኃይለማሪያም ሰይፉ የቴሌቪዥን እና የሬድዮ ድራማ አዘጋጅቷል፡፡ በበርካታ ተውኔቶች ላይ ተውኗል፤ በመነበነባንብ ፣በልብ-ወለድና ግጥም ፀሐፊነት ፤በቴአትር ሞያ አሠልጣኝነት፣በጥናታዊ ጽሁፍ አቅራቢነት፣ በጥበቡ ዘርፍ በሞያው አሻራውን ያኖረ አንጋፋ የጥበብ ሰው ነው ፡፡ ***//*** በ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ ታህሳስ 13 ቀን 2018 ዓ/ም www.ent.gov.et
አመራሩ ለውጥ ላይ ነው
አመራሩ ለውጥ ላይ ነው፡የሥራ ተነሳሽነት አለ፡ ጅምሮቹ ይኽን ያሳየሉ፡፡የተከበሩ ወርቀሰሙ ማሞ ታህሳስ 21 ቀን 2018 ዓ/ም በክብርት ወ/ሮ ወርቀሰሙ ማሞ የጤና ማህበራዊ ጉዳዮች ባህልና ስፖርት ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተመራ ልዑክ ታህሳስ 21 ቀን 2018 ዓ/ም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር በመገኘት ጉብኝትና ምልከታ አደረገ፡፡ የቋሚ ኮሚቴው አባላት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር 70ኛ ዓመቱን ተንተርሶ በቴአትር ቤቱ የተቋቋመውን የፎቶና የአልባሳት ሙዚየም ጉብኝት ተደርጓል ፤እንዲሁም በአዲሱ ቴአትር ቤት ላይ ምልከታ ያደረገ ሲሆን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር የ8 ዓመት የስኬት ጉዞ እና ወደፊት ትኩረት የሚሹ ስትራቴጂክ ጉዳዮች›› በሚል ርዕስ በቴአትር ቤቱ ዋና ዳይሬክተር በዕጩ ዶ/ር ባረከ ታደሰ የተዘጋጀ ዳሰሳዊ ምልከታ ለልዑኩ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡ አመራሩ በለውጥ ላይ ነው፡፡የሥራ ተነሳሽነት አለ፡፡ጅምሮቹ ይኽን ያሳየሉ ያሉት የተከበሩ ወርቀሰሙ ማሞ ፤ይህ ዘርፍ በዜማ፣ በጽሁፍ ፣በቴአትር፣ ሰላምን፣ አብሮነትን የሚገነባ የኢትዮጵያን ገፅታ የሚቀይር ማርሽ ቀያሪ ዘርፍ ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡ ዘርፉ የሚሰራው አዕምሮ ላይ እንደመሆኑ የኢትዮጵያን ከፍታ የሚያሳይ፤ አብሮነትንና ወንድማማችነትን የሚያመጣ በመሆኑ በዘርፉ ልንጠቀምበት ይገባል ያሉት ክብርት ወርቀሰሙ ማሞ በጉብኝቱ የተመለከቱት ሙዚየም ደስ የሚያሰኝና መደራጀቱ ትልቅ የሥራ ተነሳሽነትና ሀሳብ እንደሆነ የገለጹ ሲሆን ቴአትር ቤቱ ያሉት መረጃዎች፤የጽሁፍ ዶክመንቶች በዘመናዊ መንገድ ዲጂታላይዝድ መደረግ እንዳለበት በውይይቱ አመላክተዋል፡፡ አያይዘውም የአዲሱ ቴአትር ቤት ግንባታ ክትትልን በተመለከተ ከሚኒስትሮች ጋር በመነጋገር ድጋፍና ክትትል እንደሚደረግ ገልጸዋል፡፡ የጤና ማህበራዊ ጉዳዮች ባህልና ስፖርት ቋሚ ኮሚቴ ም/ ሰብሳቢ ዶ/ር ታደለ ቡርቃ በበኩላቸው የቴአትር ቤቱ ትልቁ ጉዳይ እና ሀብት ተመልካች ነው፤ በተመልካች ልማት ላይ ጠንክሮ መሥራት ይገባል ብለዋል፡፡ አያይዘውም የሥራ ተነሳሽነት ፣ኢትዮጵያን የመሰለ ቤት እና ባለሞያ፣ እንዲሁም ቅንጅታዊ ሥራ በተግባር የተገለጠ እንዲሆን መትጋት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ የቋሚ ኮሚቴው አባላት ማብራሪያ የሚፈልጉበትን ጉዳዮች በማንሳት ማብራሪያ የተሰጠበት ሲሆን ባሉት ጅምር ሥራዎች የተሰማቸውን ደስታ ሳይሸሽጉ ጅምሮችን አጠናክሮ መቀጠል እንደሚያስፈልግ ገልጸው ድጋፍ እና ክትትል በማድረግ ከጎናችሁ ነን ብለዋል። www.ent.gov.et








































